ከ23 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 23 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ።

የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ሲሆን÷የስድስት ወራት የኦፕሬሽን፣ የፋይናንሺያል እና የካፒታል ፕሮጀክት ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል።

በግማሽ ዓመቱ አጠቃላይ የድርጅቱን የኦፕሬሽን አገልግሎት መጠን 2 ሚሊየን 544 ሺህ 810 ቶን ለማድረስ ታቅዶ ወደ 3 ሚሊየን 674 ሺህ 242 ቶን ማድረስ እንደተቻለም ተገልጿል።

እንዲሁም በፋይናንሺያል አፈፃፀም 23 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር ገቢ እና ከታክስ በፊት 3 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘት ተችሏል ተብሏል።

ግምገማው ነገም የሚቀጥል ሲሆን÷ የቀጣይ ስራዎች አተገባበር ላይም ውይይት የሚደረግ መሆኑን የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ ያመላክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *