የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባዔና ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው

20ኛው የአፍሪካ የባለ ልዩ ጣዕም ቡናዎች ሳምንትና ኤግዚቢሽን ከጥር 28 ጀምሮ ለአምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ በመርሐ-ግብሩ ከ25 ሀገራት የተውጣጡ 800 ቡና አምራችና ገዥ ድርጅቶች ይሳተፋሉ።

መርሐ-ግብሩ ኢትዮጵያ የቡና ሃብቷን የምታስተዋውቅበት፣ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ምርታቸውን በማስተዋወቅ ለውጪ ገበያ እንዲያቀርቡ የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት እንደሚሆንም ገልጸዋል።

ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ እንግዶችም በሲዳማና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ቡና አምራች አካባቢዎችን ይጎበኛሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“ባለ ልዩ ጣዕም ቡና መገኛ” በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው ጉባዔም÷ ዓለም አቀፍ የቡና ገዥዎች፣ ምሁራንና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚታደሙ አመላክተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *