ሚኒስቴሩ በቻይና የተፈራረማቸውን ሥምምነቶች ወደ ሥራ ለማስገባት እየሠራሁ ነው አለ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቻይና ሄናን ግዛት ጄንጆ ከተማ የሳይንሥና ቴክኖሎጂ ዲቪዥን ጋር የተፈራረማቸውን ሥምምነቶች ወደ ሥራ ለማስገባት እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴዔታ ሁሪያ አሊ ÷ ከቻይና ሄናን ግዛት ጄንጆ ከተማ ከመጡ በዋንግ ዋንፔንግ የተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት ጥቅምት ወር 2016 ከላይ ከተመለከተው ዲቪዥን ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ሠነድን ሥምምነት ወደ ሥራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በሥምምነቱ መሠረትም የምርምር ሥራዎች ፣ የአቅም ግንባታ ፣ የተመራማሪና ምርምር ውጤቶች ልውውጦች እንዲሁም ዐውደ ጥናቶች በጋራ ለማካሄድ እንዲቻል በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ ጠይቀዋል።

የምርምር ሥራዎቹ በዋናነት በአካል ጉዳተኞች እና በአዕምሮ ጤና ችግር ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መፍታት ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባም ጠይቀዋል።

የትብብር ማዕቀፎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት በተቋማቸው በኩል ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።

የልኡካን ቡድኑ በተፈረመው ሥምምነት መሰረት ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፉ ገልጸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ያለው ትብብር የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *