የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ከፓኪስታኒ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑክ ቡድን ጋር ውይይት አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን መድረክ ከፓኪስታኒ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑክ ቡድን ጋር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ሀገራችን ስላላት ዕምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ለቡድኑ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን መንግስት ዘርፉን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት እና እንዲህ ያሉ መድረኮች የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ግንኙነት በማጠናከር ያላቸውን ቁልፍ ሚና አስረድተዋል፡፡

ኮምሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የግል ዘርፉን በኢኮኖሚ ተስታፊነት ለመጨመር እና ሴክተሩን ለመደገፍ በተደረጉ የህግ እና የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡

የልዑክ ቡድኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ያለውን ፍላጎት የገለፅ ሲሆን የሁለቱም ሀገራት አምባሳደሮችም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በተለያየ ዘርፍ ለማሳደግ በጋራ አንደሚሰሩ ገልፅዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *