የቻይና ኢንዱስትሪና ንግድ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለፀ

የቻይና የኢንዱስትሪ እና ንግድ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ በብረት እና ግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሚ÷ ከ17 የቻይና ኢንተርፕራይዞች ከተወጣጡ የቻይና የኢንዱስትሪ እና ንግድ ፌዴሬሽን ልዑካን ቡድን ጋር መክረዋል።

ኮሚሽነሯ በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲሁም በመንግስት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በሚሰሩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የፌዴሬሽኑ ም/ሊቀመንበር ዙ ሌጀንግ በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ገበያ እንደ መነሻ መዳረሻ ሀገር በመሆኗ ቻይና ለሀገራቱ ግንኙነት ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።

የቻይናን በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሳታፊነት ለማሳደግ በሁለቱም ሀገራት በኩል የኢንቨስትመንት ፎረም ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ በብረት እና በግብርና ዘርፎች የመስማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *