የቻይናዋ ውንሻን ከተማ ከሐረር ከተማ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

በሐረር ከተማ እና በቻይናዋ ውንሻን ከተማ መካከል የእህትማማችነት ግንኙነት መመስረት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ ኢትዮጵያ እና ቻይና ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ጠንካራ የትብብር ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተዋል።

በዚህም ቻይና በተለያዩ ዘርፎች በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሰላም እና በልማት ዙሪያ ድጋፍ በማድረግ እያከናወነች ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

ሐረር ከተማ የጁገል ቅርስን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ዓለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ መሆኗን ጠቁመው፣ በዩኔስኮ በሰላም፣ በመቻቻል እና በአብሮነት ከተማነት ዓለም አቀፍ ሽልማት እና እውቅናን ማግኘቷን አስታውሰዋል።

ሐረር ከተማ ከቻይናዋ ውንሻን ከተማ ጋር የእህትማማችነት ግንኙነት ለመመስረት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት በበይነ መረብ መካሄዱንም ጠቅሰዋል።

በውይይቱ ባሕልን ለማስተዋወቅ፣ ታሪካዊ ቅርሶችንና ሙዚዬሞችን ለመጠበቅና እንክብካቤ ለማድረግ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙኑት ለማጠናከርና፣የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለማጎልበት በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት ከቻይናዋ ውንሻን ከተማ ጋር በቅንጅት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸው፣ የውሻን ከተማ ከክልሉ መንግስት ጋር ለመስራት ያለውን ዝግጁነትም አድንቀዋል።

የቻይናዋ ውንሻን ከተማ አመራሮች በበኩላቸው፣ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረ እና በመልካም ወዳጅነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የልዑካን ቡድናቸው የውንሻን ከተማን እንዲጎበኙ መጠየቃቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *