በኢትዮጵያ የዲጅታል የክፍያ አማራጭ በመስፋፋቱ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ዶ/ር ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የዲጅታል የክፍያ አማራጭ በመስፋፋቱ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ዶ/ር ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ በዲጂታል የክፍያ አማራጮች አማካኝነት በዓመት እስከ አራት ትሪሊዮን ብር እየተዘዋወረ መሆኑን አስታውቀዋል። እዮብ ተካልኝ ዶ/ር ሁለተኛውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፤ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ባለፉት ሁለት ወራት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን አንስተዋል።

ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተተገበሩ በመሆኑ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ሊቀንስ እንደቻለ አመላክተዋል። በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ ነው ያሉት ዶክተር እዮብ፤ በዓመት እስከ አራት ትሪሊዮን የሚደርስ ብር በዲጂታል የክፍያ አማራጮች እንደሚዘዋወር አመላክተዋል።
መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብ ልውውጥ የሚደረግባቸው ግብይቶች በዲጂታል እንዲከናወኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከ 170 በላይ የመንግሥት ተቋማት የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ውስጥ መግባታቸውን አስታውሰዋል።
 
የኢትዮጵያን ዘመናዊ የፋይናንስ ሥርዓት ግብ ለማሳካት በመንግሥት አገልግሎቶች፣ በንግድ ሥራዎች የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮችን በዲጅታል የክፍያ አማራጮች መጠቀምና የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ማስቀረት ይገባል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ ሰዎች የዕለት ተዕለት ግብይታቸውን ጥሬ ገንዘብ ይዘው መሄድ ሳያስፈልጋቸው በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የሚፈልጉትን ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል።

Source: APA

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *