በቻይና በተዘጋጀው የአፈር ጤንነት አጠባበቅ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ተሳተፈች።

በቻይና በተዘጋጀው የአፈር ጤንነት አጠባበቅ መድረክ እና በቻይና የአፍሪካ ቀንድ የግብርና ትብብር አውደ ጥናት ላይ ኢትዮጵያ ተሳተፈች ነው።

በመድረኩ የአፈር ጤንነት በአለም ዓቀፍ ደረጃ አሳሳቢ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ በዓለም ደረጃ ትብብር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

በተመሳሳይ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቻይና ያንግሊንግ በተካሄደው የቻይና የአፍሪካ ቀንድ የግብርና ትብብር አውደ ጥናት ላይ የተሳተፈ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ በአውድ ጥናቱ አቅርቧል።

የኤምባሲው ተወካዮች የኢትጵያ መንግስት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት እየተገበረ ያለውን የግብርና መር ኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአውደ ጥናቱ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ተወካዮች፣ ከአለም አቀፍ ተቋማትና ከግል ሴክተሮች ከየተወጣጡ ከ160 በላይ ልዑካን መሳተፋቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *