ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን ባለብዙ ዘርፍ የእድገት አላማ ብሎም የተገኙ ድሎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም ከቻይና ጋር የንግድ ግንኙነቶችን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *