የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በሙሉ ዐቅሙ ሥራ መጀመር የሚያስችል ቁመና ላይ መሆኑ ተገለጸ

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በሙሉ ዐቅሙ ሥራ ለመጀመር በሚያስችል ቁመና ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ቀጣናው የሎጂስቲክስ፣ የንግድ እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እንዲሁም ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለማስተናገድ የሚችልበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና የሚገኙና በተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የተሠማሩ ኢንቨስተሮች ያሉበትን የምርት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም÷ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቀጣናው ውጤታማ እንዲሆንና በሙሉ ዐቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ነፃ የንግድ ቀጣናው በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ተኪ ምርቶችን በማምረት፣ በቴክኖሎጂና ዕውቀት ሽግግር ባለፈው አንድ ዓመት ያስመዘገበው ውጤት የሚደነቅ መሆኑን መናገራቸውን የኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል።

ቀጣናው በቅርቡ በሙሉ ዐቅሙ ሥራ እንዲጀምርም÷ በሎጂስቲክስ፣ ገቢና ወጪ ንግድ ዙሪያ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና አሁን ላይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ባለሀብቶችን እያስተናገደ መሆኑም ተመላክቷል።

እንዲሁም በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ለተወካዮች ምክር ቤት የተላከው የልዩ ኢኮኖሚክ ዞን አዋጅ ሲፀድቅ÷ በንግድ፣ በሎጂስቲክስ፣ በገቢና ወጪ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ባለሀብቶችን መቀበል እንደሚጀምር ነው የተጠቆመው።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *