የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ 28 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ አቀረበ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ28 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ።

በሌላ በኩል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ850 ለሚልቁ ወገኖች አዲስ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አሕመድ ሰዒድ ገልፀዋል።

እንዲሁም በውጪ ምንዛሪ ወደ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ተኪ ምርቶችን በማምረት ፓርኩ ከ350 ሺህ ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ከ67 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡና ለምርት ሂደት የሚረዱ ግብዓቶች ቀርበዋል ማለታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል።

ፓርኩ አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሥራውን በመከወን ከ38 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱንም አስረድተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *