የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ በቻይና ጉዋንዱንግ ግዛት ምክትል ሊቀመንበር ዋን ባኦቺንግ የተመራ ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገርዋል

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሃመድ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዳለና እስካሁንም በርካታ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ገቢን በማሳደግ፣ በስራ እድል ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸው በቀጣይም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ቻይና ላደረገችው ድጋፍ ሚንስትር ዴኤታው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብና ነባሮቹን ለማስፋት በሚደረጉ ጥረቶች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል።

ምንጭ፦ የኢንደስትሪ ሚኒስተር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *