የኢትዮጵያ ድርጅቶች በቻይና ዓለም አቀፍ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፉ ነው

የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ የኢትዮጵያ ድርጅቶች በቻይና ዓለም አቀፍ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በሻንጋይ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ኤክስፓ ላይ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን እያስተዋወቁ መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ኤክስፖው ከተለያዩ ከተሞች ከመጡ ሰዎች በተጨማሪ በተለያዩ የቻይና የንግድ ተጠሪ ድርጅቶችና በማህበራት ሃላፊዎች መጎብኘቱ ተጠቅሷል።

ከኤክስፖው ጎን ለጎን በሚካሄዱ የማስተዋወቂያ መድረኮች ላይ የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ የወጪ ምርቶች እና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ መቻሉም ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *