የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት 1 ሺህ 585 ፍቃዶችን ሰጠ

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት በንግድ ምልክት፣ በፓተንት፣ የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ 585 ፍቃዶችን ሰጠ።

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኤልያስ ጥሩነህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ተቋሙ ፈቃዱን የሰጠው በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ውስጥ ነው።

በዚህም ንግድ ምልክት፣ ፓተንት ፍቃድና ኢንዱስትሪያል ዲዛይንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ፍቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል።

በተለይም ፍቃድ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል በንግድ ምልክት ብቻ 1 ሺህ 8 ፍቃዶች ተሰጥተዋል።

በተጨማሪም 16 በፓተንት ፍቃድ፥ 102 በአገልግሎት ሞዴል እንዲሁም 65 በኢንዱስትሪያል ዲዛይን ፍቃድ መስጠቱን ተናግረዋል።

በተለይም ተቋሙ በአስገቢ ፓተንት 20 ፍቃድ የሰጠ ሲሆን፥ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ደግሞ 374 ፍቃዶችን ሰጥቷል።

በሌላ በኩል ተቋሙ በተመዘገቡ የአእምሯዊ ፈጠራ መብቶች ላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የመብት ጥሰት እንዳይፈጸም በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ መሆኑም ተጠቅሷል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *