የብድር ሁኔታ በተመለከተ ያለው ማዕቀፍ በፍጥነት ስለሚሻሻልበት ሁኔታ ምክክር ተደረገ

የብድር ሁኔታ በተመለከተ ያለው ማዕቀፍ በፍጥነት ስለሚሻሻልበትና የብድር እፎይታ ሂደትን ስለሚሰጥበት ሁኔታ ምክክር ተደረገ።

የቡድን 20 የወቅቱ ፕሬዚዳንት የሆነችው ብራዚል፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ በትብብር ያዘጋጁት የዓለም ዓቀፍ የሀገራት የብድር ውይይት መድረክ ላይ ተካሂዷል።

በመድረኩ 22 አባላት ያሉት የፓሪስ ክለብ ሀገራት፣ የፓሪስ ክለብ አባል ያልሆኑ አበዳሪ ሀገራት፣ ተበዳሪ ሀገራት እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የብድር የጋራ ማዕቀፍን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ላይ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል።

አበዳሪዎችና አጋሮች የብድር አከፋፈል ሁኔታን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት ሚኒስትሩ ማድነቃቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

በተለይም የብድር ጫና ያለባቸው አካላት እፎይታ የሚያገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ ከአበዳሪወች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ የብድር አከፋፈል ማሻሻያ ማዕቀፉ ስላለው ጠቀሜታ ተናግረዋል።

በመድረኩ በዓለም ላይ ከብድር ጫና ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ለመፍታት በትብብር እየተሰራ ያለውን ስራ በማጠናከርና ድጋፍ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት መደረጉ ተገልጿል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *