የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሺየቲቭ ለድህነት ቅነሳ አስተዋፅኦ ማድረጉን ቻይና ገለጸች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አለም ዓቀፉ የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሺየቲቭ በዓለም ላይ ድህነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ አስተዋጽኦ ማድረጉን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተቴር አስታወቀ።

የቻይና የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፤ “ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” የተባለው የቻይና ትብብር ለድህነት ቅነሳ ፕሮገራም ያደረገውን አስተዋፅኦ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የ2013 ዘላቂ ልማት አጀንዳ ዋና ግብ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከ10 ዓመት በፊት ይፋ የተደረገው የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሺቲቭ ለድህነት ቅነሳ ቅድሚያ በመስጠት በዓለም ዓቀፍ ትብብር በኩል እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ባለፉት አስርት ዓመታት ከ1 ትሪሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ፈሰስ በማድረግ እና መንገድን በማስፋፋት 40 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት ማውጣቱን ገልፀዋል።

በተለይም ፕሮጀክቱ በሚያከናውናቸው የግብርና ትብብር ስራዎች በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ህዝቦች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ሰብዓዊ ድጋፎችን እንዲያገኙ ማስቻሉን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም በቤልት ኤንድ ሮድ ፕሮጀክት ማዕቀፍ ስር የሚገኙ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት እና የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በአለም ዓቀፍ ደረጃ በርካታ የስራ እድሎችን ፈጥረዋል ማለተቻውን ዢንዋ ዘግቧል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *