የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ6 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ላስመዘገቡ ባለሐብቶች ፈቃድ ተሰጠ

በተጠናቀቀው ስድስት ወር 6 ነጥብ 857 ቢሊየን ብር ሐብት ላስመዘገቡ ባለሐብቶች ፈቃድ መስጠቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ፈቃድ የተሠጠባቸው ዘርፎችም ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት መሆናቸውን የቢሮው ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በግብርና ለ68፣ በኢንዱስትሪ ለ44፣ በአገልግሎት ለ20 በድምሩ ለ132 ባለሐብቶች ፈቃድ መሰጠቱንም ነው የገለጹት።

ፈቃድ የተሰጠባቸው ፕሮጀክቶችም ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ÷ 9 ሺህ 294 ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ አስረድተዋል።

በተጨማሪም 13 ሺህ 742 ጊዜያዊ የሥራ ዕድ እንደሚፈጥሩ አመላክተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *