![](https://onestopinvestmentservices.com/wp-content/uploads/2023/11/commm-1-750x430-1.jpg)
የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት አራት ወራት 64 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 95 በመቶ ማሳካቱን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በአራት ወራት የተከናወኑ ሥራዎችን የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል።
በገቢ አሰባሰብ፣ ኮንትሮባንድ እና ሕገ- ወጥ ንግድን በመከላከል ረገድ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ናቸው መባሉን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ÷ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይ ወራትም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አመላክተዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.