ክልሉ ከ5 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት ሶስት ወራት ከ5 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የክልሉ ቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አስራት መኩሪያ÷ ከ1 ሺህ 300 ቶን በላይ የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን አስታውቀዋል።

በ2016 ዓ.ም ከ54 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱን ጠቅሰው፤ ባለፉት ሶስት ወራት ከ5 ሺህ ቶን በላይ ቅመማ ቅመም ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ጠቁመዋል።

በቅመማ ቅመም ግብይት የሚስተዋለውን ተግዳሮት መፍታት የሚያስችል የማስፈጸሚያ ሕገ ደንብ መዘጋጀቱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በክልሉ ከፍተኛ የሻይ ምርት እንዳለ አመልክተዋል።

ባለፈው አመት ከ7 ሺህ ቶን በላይ የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን አስታውሰው፤ ዘንድሮ 7 ሺህ 26 ቶን የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *