ኤም ቲ ኤን  በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

የተርኪዬው ኤም ቲ ኤን ኢንተርናሽናል መንግስታዊ ኩባንያ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።

በተርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አደም መሐመድ ኤም ቲ ኤን ኢንተርናሽናል ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኒል ይለድሪም እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኒል ይልድሪም ተርክዬ እና ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ባደረጉት ስምምነት መሰረት በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ ገልጸዋል።

ለዚህም በተርኪዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮን ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

አምባሳደር አደም በበኩላቸዉ ቀደም ሲል በተፈረመዉ ስምምነት መሰረት ወደ ተግባር መግባት ጠቃሚ መሆኑን በማንሳት የኢትዮጵያን የማእድን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ገልጸዋል።

ኤም ቲ ኤን ኢንተርናሺናል ኩባንያ በተርኪዬ ሪፐብሊክ ኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርን በመወከል የማዕድን ምርምር፣ ፍለጋ እና ሌሎች ተግባራትን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያከናዉንና እኤአ በ2019 የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን በቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ሚሲዮን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *