ኢትዮጵያ የቢትኮይን ግብይት ማካሄድ የሚያስችል መረጃ ማዕከል ግንባታ ስምምነት ተፈራረመች።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲን ከሆንግ ኮንግ ኩባንያ ጋር የ250 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርሟል

በኢትዮጵያ የምናባዊ ግብይትን ማካሄድ አሁንም እንደተከለከለ ነው

ኢትዮጵያ የቢትኮይን ግብይት ማካሄድ የሚያስችል መረጃ ማዕከል ግንባታ ስምምነት ተፈራረመች።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምናበዊ ገንዘብ ወይም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ፍላጎት እየጨመረ ሲሆን በኢትዮጵያም አጀንዳ ከሆነ አምስት ዓመት ሆኖታል።

ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኛውንም የምናባዊ ገንዘብ ግብይት ወይም ክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት እንዳልፈቀደ እና ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ ሰዎችም በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቆ ነበር።

ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ የቢትኮይን ግብይት መፈጸም የሚያስችሉ መሰረተ ልማት ግንባታ የሚያደርጉ ኩባያዎች ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።

ኢትዮጵያ አሁንም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት እንዲደረግ ያልፈቀደች ሲሆን የዳታ ማዕከል ግንባታዎች እንዲካሄዱ ግን ስምምነቶችን በመፈራረም ላይ ነች።

በዛሬው ዕለትም ዌስት ዳታ ማዕከል የተሰኘው ኩባንያ የ250 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር ተፈራርሟል።

በዚህ ስምምነት መሰረት የቢትኮይን ግብይት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት የሚያስችሉ እንደሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ርካሽ የኤሌክትሪክ ሽያጭ አለኝ በሚል ዓለም አቀፍ የመረጃ ማዕከል ኩባንያዎችን ለመሳብ እየጣረች ሲሆን የእስያ ክሪፕቶ ከረንሲ ኩባንያዎች ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ስምምነቶችን እየተፈራረሙ ናቸው።

ብሉምበርግ ባሳለፍነው ሳምንት እንዳስነበበው 21 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ኢትዮጵያን የመረጡት ርካሽ የሀይል ሽያጭ እና ቻይና ምናባዊ ገንዘብ ግብይትን በመከልከሏ ምክንያት ነው።

በዓለም ላይ ካሉ ምናባዊ የመገበያያ ገንዘብ ተቋማት መካከል ግማሽ ያህሉ በአሜሪካ ቴክሳስ የከተሙ ሲሆን በቀን በአማካኝ 2 ሺህ 300 ሜጋ ዋት ሀይል የሚጠቀሙ ሲሆን የሀይል ፍጆታ ዋጋ ታሪፍ ከፍተኛ መሆኑ ኩባንያዎቹ ወደ ሌሎች ሀገራት በመዞር ላይ ናቸው ተብሏል።

የሩሲያ እና ቻይና ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የዳታ ማዕከላቸውን ለመክፈት ፍላጎታቸው ከፍተኛ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የአይሲቲ ፓርክ ውስጥ የዳታ ማዕከላትን ለመገንባት ስምምነቶችን እየተፈራረሙ ናቸው።

የዓለም ክሊፕቶከረንሲ ፍላጎት እየጨመረ የመጣ ሲሆን አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ51 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ይገኛል ተብሏል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *