ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ኩባንያ ምርት ለማስጀመር እየተሰራ ነው::

የማዕድን ሚኒስት ክቡር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጅሉ እና የማዕድን ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በጋምቤላ ክልል በዲማ ወረዳ የሚገኘውን የኢትኖ ማይኒንግ ኩባንያን የስራ እቅስቃሴ ተመልከተዋል::

ኢትኖ ማይኒንግ ኩባንያ ከአስር አመት በላይ በጋምቤላ ክልል በዲማ ወረዳ የወርቅ ፍለጋ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል::

ኩባንያው የወርቅ ማምረት ፈቃድ ወስዶ ወርቅ ለማምረት የፋብሪካ ተከላ እና ሌሎች ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ እስካሁን ያለው አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሁለት ወራት ውስጥ የፋብሪካ ተከላውን አጠናቆ ወደ ምርት እንዲገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በሌላ በኩል በክልሉ በባህላዊ እና በልዩ አነስተኛ እየተመረተ ያለው የወርቅ ምርት ያለበትን ሁኔታ ከክልሉና ከወረዳዎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ተገምግሟል፡፡

ችግሮቹን በመፍታት በሚቀጥሉት ወራት የተሻለ የወርቅ ምርት ለማስገባት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *