አዲሱ የንግድ ህግ ከ25 እስከ 50 ዓመት እንዲያገለግል ሆኖ መዘጋጀቱ ተነገረ

የኢንቨስትመንት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣት፣ አከባቢያዊና አለምአቀፋዊ የንግድ ትስስር መጎልበት ለአዲሱ የንግድ ህግ መዉጣት መነሻ ምክንያቶች መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን ይህን ታሳቢ አድርጓል የተባለዉ አዲሱ ስርዓት ከ25 ዓመታት በላይ ሊያገለግል እንደሚችል ተዘግቧል።

በ1952 ዓ.ም. የወጣዉ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ ለ60 ዓመታት ካገለገለ በኃላ የተተካው በ2013 እንደነበር ይታወቃል።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ  አቶ ይርሳው ዘውዴ እንደተናገሩት “በ1952 ዓ.ም. የንግድ ህግ በዘመኑ ጊዜውን የቀደመ ቢሆን አሁን ላይ ካለው ነበራዊ ሁኔታ ጋር ደግሞ መሻሻችን የሚፈልግ ነዉ” ብለዋል።

አዲሱ የንግድ ህግ አለም አቀፋዊ ሁኔታው  ተለዋዋጭ መሆኑን ግምት ውስጥ ያስገባና የሚፈጠሩ ለውጦችን ተከትሎ እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻያዎች እየተደረገበት ቢያንስ ከ 25 እስከ 50 ዓመት ድረስ እንዲያገለግል ታስቦ ጊዜ ተወስዶና በጥናት ላይ ተመስርቶ የወጣ ህግ መሆኑም ካፒታል ሰምቷል።

ምንጭ፦ ካፒታል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *