ንግድ ባንክ በሲቢኢ ኑር አገልግሎት ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ሂሳብ ሰበሰበ::

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ በሲቢኢ ኑር የባንክ አገልግሎት ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ሂሳብ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሲቢኢ ኑር) የጀመረበትን 10ኛ ዓመት በጅማ ከተማ አክብሯል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ኑሪ ሁሴን እንደገለጹት÷ ባለፉት 10 ዓመታት በሲቢኢ ኑር 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ደንበኞችን ማፍራት ተችሏል፡፡

የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበትም በባንኩ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከደንበኞች ጋር ውይይት ተደርጓል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *