ቻይና የቤልት ኤንድ ሮድ ትብብርን በጥራት ለመተግበር ያስችለኛል ያለችውን ዕቅድ ይፋ አደረገች

የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የ”ቤልት ኤንድ ሮድ” ትብብርን በከፍተኛ ጥራት ለመተግበር ያስችላል ያሉትን የሀገሪቱን ዕቅድ ሥምንት ደረጃዎች ይፋ አደረጉ።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዕቅዱን ይፋ ያደረጉት በቤጂንጉ ሦስተኛው የ”ቤልት ኤንድ ሮድ” ዓለምአቀፍ የትብብር መድረክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የቻይና ልማት ባንክ እና የቻይናው የወጪ–ገቢ ባንክ እያንዳንዳቸው 350 ቢሊየን ዩዋን (48 ነጥብ 75 ቢሊየን ዶላር) መድበው እንደሚንቀሳቀሱ ፕሬዚዳንት ሺ ተናግረዋል።

በተጨማሪም 80 ቢሊየን ዩዋን ለ”ሲልክ ኤንድ ሮድ” ፕሮጀክት ፈሰስ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።

በመርሐ-ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር ያደረጉ ሲሆን የቻይና እና የአፍሪካ አኅጉር ታሪካዊ ግንኙነት እና ዕድገት ላይ ገለጻ አድርገዋል።

የ”ቤልት ኤንድ ሮድ” መድረክም የቻይና – አፍሪካን ትብብር በማጠናከር ረገድ መሠረት መጣሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አንስተዋል።

የአፍሪካን ተፅዕኖ ፈጣሪነት እንደ “ቤልት ሮድ” ባሉ የባለ-ብዙ ወገን የትብብር መድረኮች በመሳተፍ ማረጋገጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *