በ2024 ከዶላር አንጻር ደካማ ገንዘብ ያላቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለቀወ ዋጋ ጥንካሬውንና ድክመቱን ያሳያል።

ሳኦቶሜና ፐሪንሲፔ ቀዳሚ ስትሆን፤ 1 የዶላር በ22 ሺህ 281 የሀገሪቱ ገንዘብ (ዶቦራ) ይመነዘራል

በፈረንጆቹ 2024 ከዶላር አንጻር ገንዘባቸው ደካማ የሆነ 10 የአፍሪካ ሀገራት ከሰሞኑ ይፋ ተደርገዋል።

የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለው ዋጋ ጥንካሬውን እን ድክመቱን ያሳያል የተባለ ሲሆን፤ ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ከሰሞኑ ከከዶላር አንጻር ገንዘባቸው ደካማ የሆነ 10 የአፍሪካ ሀገራትን ይፋ አድርጓል።

ከአፍሪካ ከዶላር አንጻር ደካማ ገንዘብ ያላት ቀዳሚ ሀገር ሳኦቶሜና ፐሪንሲፔ ነች የተባለ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር 22 ሺህ 281.8 የሀገሪቱ ገንዘብ (ዶቦራ) ይመነዘራል።

የስራሊዮን ገንዘብም ከዶላር አንጻር ደካማ ከሚባሉት ውስጥ 2ኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ19 ሺህ 678 ሴራሊዮን ገንዘብ (ሊዮን) ይመነዘራል።

የጊኒ ገንዘብም በ3ኛ ደረጃ የያዘ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ8 ሺህ 583 የሀገሪቱ ገንዘብ (ጊኒ ፍንክ እንደሚመነዝርም ተመልክቷል።

4ኛ ደረጃ ላይ የተመቀጠው የማዳካስካር ገንዘብ ሲሆን፤ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ4 ሺህ 528.28 የማዳካስካር ማጋላሳይ አሪራይ እየመተመነዘረ መሆኑ ነው የተነገረው።

የኡጋንዳ ሺሊንግ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል የተባለ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ሶላር በ3 ሺህ 849 የኡጋንዳ ሺልንግ ይመነዘራል ነው የተባለው።

6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የቡሩኑዲ ገንዘብ ነው፤ በዚህም 1 የአሜሪካ ዶላር በ2 ሺህ 849 የቡሩንዲ ፍራንክ ነው የሚመነዘረው ይላል መረጃው።

የዲሞክራክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ገንዘብም 7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር 2 ሺህ 752 የኮንጎሊዝ ፍራንክ ነው የሚመነዘረው።

የታንዛኒያ ገንዘብ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ2 ሺህ 540 የታንዛኒያ ሺሊንግ እንደሚመነዘር ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ያላዊ ገንዘብ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ1 ሺህ 680 የማዊ ከዋቻ እንደሚመነዘርም ተነግሯል።

የናይጄሪያ ገንዘብ 10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ1 ሺህ 500 የናይጄሪያ ናይራ እንደሚመነዘርም ነው የተገለጸው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *