በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዓለም አቀፍ ሰሊጥ ኮንፈሬንስ ላይ ተሳትፎ አደረገ

የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር በሻንዶንግ ፕሮቪንስ በቺንዳሆ ከተማ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 15 እስከ 17 ቀን 2024 በተካሄደ ‘’China International Sesame Conference’’ ላይ ተሳትፎ በማድረግ የሀገራችንን የሰሊጥ ምርት አስተዋውቀዋል።

ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር በኮንፈረንሱ ባደረጉት ንግግር ከሀገራችን ወደ ቻይና የሚላክ የሰሊጥ ምርት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ቅናሽ ማሳየቱን ጠቅሰው በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ የተመረተው የሰሊጥ ምርት ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ቻይና የሚላክ ምርት ሊጨምር እንደሚችል አንስተዋል።

ክቡር አምባሳደሩ ከቻይና የሰሊጥ ማህበር ፕሬዚዳንት ጋርም በመስኩ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በኮንፈረንሱ ከ300 በላይ በመስኩ የተሰማሩ ኩባንያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን፣ የዓለም አቀፍ የሰሊጥ ዋጋ ሁኔታ በተመለከተም ውይይት ተደርጓል። የኢትዮጵያ የሰሊጥ ላኪዎች ማህበር ተወካይና የቦርድ አባል የሀገራችንን የሰሊጥ ምርት ሁኔታ በተመለከተ ለታዳሚዎች ጹሑፍ አቅርበዋል። በኮንፈሬንሱ 15 በሀገራችን በሰሊጥ መስክ የተሰማሩ ነጋደዎች ተሳትፈው ከቻይና ባለሀብቶች ጋር የንግድ ትስስር ፈጥረዋል።

Embassy of Ethiopia, Beijing

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *