በቱሪዝም ዘርፍ  ዙሪያ ከዓየር መንገዱ ጋር በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደረገ

 የቱሪዝም ሚንስትር ዴዔታ ሌንሳ መኮንን ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ጋር በቱሪዝም ዘርፍ  ዙሪያ በሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

በውይይታቸውም÷ የጎብኚ ፍሰቱን ለመጨመር በቅንጅት ለመሥራት እና እስከአሁን እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

እንዲሁም እንደ “ET-Holiday” ዓይነት የጎብኚ ማበረታቻ መርሐ-ግብሮችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተግባብተዋል።

በዓመት ከ 11 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግደው ዓየርመንገዱ÷ ደንበኞቹ ስለኢትዮጵያ የጎብኚ መዳረሻዎች መረጃ እንዲኖራቸውና የተለያዩ የሀገሪቱን አካባቢዎች እንዲጎበኙ ለማድረግ ብሎም አዳዲስ የቱሪዝም ፕሮሞሽን መንገዶችን ለመጠቀም በሚቻልበት አግባብ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *