በቱሪዝሙ ዘርፍ ከሞሮኮ ጋር ለመሥራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደረገ

 የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ሌንሳ መኮንን ከሞሮኮ አምባሳደር ነዝሀ አላው ጋር በቱሪዝሙ ዘርፍ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይታቸውም÷ ሞሮኮ በሰው ኃይል ሥልጠና ድጋፍ እንድታደርግ ከስምምነት ተደርሷል።

በተጨማሪም በቱሪዝም ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ላይ ሞሮኮ ያላትን ልምድ ለአመራሮች እና ለባለሙያዎች እንድታካፍል መስማማታቸው ተገልጿል።

የቱሪዝም ስትራቴጂ እና አተገባበሩ ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግም ከስምምነት መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

በርካታ ዕሴቶችን በሚጋሩት ሐረር ከተማ እና በሞሮኮዋ ፌስ ከተማ መካከል የእህትማማች ከተማ ሥምምነት ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *