በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው

በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች በግል አልሚዎች እየለሙ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው።

አምባደሮች በፌዳ ዋቅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጎልድ የኢንዱስትሪ መንደርን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር ባጫ ደበሌ፣ አምባሳደር ሌንጮ ባንቲ፣ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶችም ተሳትፈዋል።

የጉብኝታቸው አላማም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለተቀረው ዓለም ማስተዋወቅ፣ የሀገር ውስጥ አልሚዎችን ከተወከሉባቸው ሀገራት ባለሀብቶች ጋር ማስተሳሰርና የኢንቨስትመንት ዲፕሎማሲን ማጠናከር ነው ተብሏል፡፡

ጉብኝቱ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *