በቀጣዮቹ ሳምንታት ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ እንደሚደርስ ተጠቆመ

 በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት 1 ሚሊየን 274 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርስ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመላከተ።

ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥም 510 ሺህ ኩንታል ዩሪያ የጫነች ‘አባይ ፪’ መርከብ ጂቡቲ መድረሷም ተጠቅሷል።

እስከአሁንም 9 ሚሊየን 395 ሺህ 606 ኩንታል ማዳበሪያ ወደብ መድረሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

ከዚህ ውስጥም 8 ሚሊየን 731 ሺህ 403 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑ ተመላክቷል።

በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታትም 834 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ እና 440 ሺህ ኩንታል ዩሪያ በአጠቃላይ 1 ሚሊየን 274 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *