በመዲናዋ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ከሲጂሲኦሲ የግንባታ ተቋራጭ ጋር ስምምነት ተፈረመ

ከዓለም ባንክ በተገኘ የ145 ሚሊየን ዶላር በአዲስ አበባ ከተማ የምስራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ከሲጂሲኦሲ የግንባታ ተቋራጭ ጋር ስምምነት ተፈረመ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሮጀክቱ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ፕሮጀክቱ በዋነኛነት ከዚህ ቀደም የፍሳሽ መሰረተ ልማት ያልተዳረሰባቸው የካ፣ ቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ ለህዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር እየፈፀምን በትጋት ማገልገላችንን የምንቀጥል ይሆናል ያሉት ከንቲባዋ፤ የዓለም ባንክ እያደረገ ላለው አስተዋፅዖም ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *