ሺ ጂንፒንግ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋገጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን በቻይና ታላቁ የሕዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ።

በውይይታቸውም÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቻይና ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ አንስተዋል።

አክለውም በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች ማለትም÷ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አይሲቲ፣ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ብሪክስን በመቀላቀሏ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል።

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ- ግብርን ያደነቁት ፕሬዚዳንቱ÷ ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *