ከተለያዩ የጃፓን አምራች ኢንዱስትሪዎች የተወጣጣ የጃፓን የልዑክ ቡድን አዲስ አበባ ደረሰ

ከተለያዩ የጃፓን አምራች ኢንዱስትሪዎች የተወጣጣ የጃፓን የልዑክ ቡድን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽንን በመጎብኘት ከምክትል ኮምሽነር ተመስገን ጥላሁን ጋር ምክክር አድርጓል።

ምክትል ኮምሽነር ተመስገን በተለይም በመንግስት ቅድሚያ ተሰጥቶዋቸው እየተሰራባቸው ባሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እና ከሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በጥምረት መሰራት በሚቻሉ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች ዙሪያ ለቡድኑ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

የልዑክ ቡድኑ አባላት በሀገራችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በፋይናንስ፤ በአምራች ዘርፉ ፤ በቴሌኮም ፤ በአይሲቲ እና በአውቶሞቲቭ ዘርፎች ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸው በዘርፉ በህግ እና በፖሊሲ ዙሪያ ያላቸውን ጥያቄዎች አንስተዋል።

ምክትል ኮምሽነሩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ኮምሽኑ ቡድኑ በሀገራችን ለሚኖሩት ፕሮጀክቶች ሙሉ ድጋፉን እንደሚስጥ ያረጋገጡ ሲሆን ቡድኑ በሀገራችን የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስተመንት ዕድል እና አማራጮችን በጥልቀት እንዲቃኙ ጋብዘዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *