ከማዕድን ወጪ ንግድ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ።

ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ወጪ ንግድ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

ገቢው ለውጪ ገበያ ከቀረቡ የወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም ኦር፣ ጌጣጌጥና የኢንዱስትሪ ማዕድናት የተገኘ መሆኑ ተገልጿል።

ሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ግብይትን ለመቅረፍ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ እንደሚከናወን መጠቆሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *