ቻይና የስድስተኛውን ትውልድ ኔትወርክ መጀመር የሚያስችል ሳተላይት ይፋ አደረገች

ሀገሪቱ ዓለም አምስተኛው ትውልድ ኔትወርክን አጥጥሞ ሳይጨርስ ስድስተኛውን ለመሞከር ዝግጅት ጀምራለች።

መንግስታዊው ቻይና ሞባይል ከፍተኛ ዳታ መልቀቅ የሚያስችል ሳተላይቱን አምጥቋል

ቻይና የስድስተኛውን ትውልድ ኔትወርክ መጀመር የሚያስችል ሳተላይት ይፋ አደረገች።

የዓለማችን ቴክኖሎጂ መሪ የሖነችው ቻይና ስድስተኛው ትውልድ ወይም 6ጂ የተሰኘውን ኔትወርክ ማቅረብ የሚያስችል ሳተላይት ማምጠቋን አስታውቃለች።

ቻይና ሞባይል በተባለው የቴሌኮም ኩባንያ በኩል የመጠቀችው ይህች የኮሙንኬሽን ሳተላይት በተሳካ ሁኔታ ህዋ ላይ ማረፏን ሽንዋ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ የመጠቀችውን ሳተላይት መሰረት በማድረግ የስድስተኛው ትውልድ ኢንተርኔት ኔትወርክ ሙከራ በቅርቡ ይጀመራል ተብሏል።

ዓለም በቀርቡ የተዋወቀውን የአምስተኛው ትውልድ ወይም 5ጂ ኔትወርክን አጣጥሞ ሳይጨርስ ቻይና አዲስ ኔትወርክ ለዓለም ለማስተዋወቅ ስራ መጀመሯ ተገልጿል።

የቻይና ሳተላይት ሙሉ ለሙሉ ሀገር በቀል በሆኑ ምርቶችን ጥጠቀማለች የተባለ ሲሆን ብልሽት ቢያጋጥም በቀላሉ መጠገን፣ ቦታ እንድትቀይር እና ሌሎች ማሻሻያዎችን ለማድረግ ምቹ ነችም ተብሏል።

በቻይና ሞባይል እና በቻይና ሳይንስ አካዳሚ ተሰርታለች የተባለችው ይህች ሳተላይት ለመሬት ቅርብ በሆነ ስፍራ ላይ በመገኘቷ ለዓለም አስተማማኝ እና ያልተቆራረጠ ኢንተርኔት ኔትወርክ ማቅረብ ያስችላታልም ተብሏል።

የቻይና ኩባንያ ለ50 አመታት የሚያገለግል “አቶሚክ ባትሪ” ሰርቷል

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ የቻይና ጠፈር ሳይንስ ተመራማሪዎች የኮሙንኬሽን መሳሪያዎችን ወደ ጠፈር ልከው ብርሃን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወር የሚያስችል ሙከራቸው እውን መሆኑን ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

አምስተኛውን ትውልድ ኢንተርኔት ለዜጎቻቸው ቀድመው ፉክክር ውስጥ የነበሩት ምዕራባዊያን ሀገራት በቻይና እንዳይቀደሙ መሰረታቸውን ቤጂንግ ያደረጉ የቴሌኮም ኩባንያዎች ላይ ማዕቀቦችን ሲጥሉ ነበር።

አሁን ደግሞ ሌላው ዓለም ዝግጅት በማያደርግበት ሁኔታ ቻይና ቀድማ ስድስተኛውን ትውልድ ወይም 6ጂ ኔትወርክ ለዓለም ለማስተዋወቅ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

ኢትዮ ቴሌኮም ከአንድ ዓመት በፊት የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎቱን ያስተዋወቀ ሲሆን በአዲስ አበባ በተመረጡ አካባቢዎች አገልግሎቱን አቅርቤያለሁ ብሏል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *