የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ::

በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ በሴዑል በተካሄደው 2ኛው የኮሪያ-አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ትብብር መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

አምባሳደር ደሴ መድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የውጭ ኢንቨስትመንት የትኩረት መስኮች እና በኢትዮ-ኮሪያ የትብብር መስኮች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር እንዳለ ጠቅሰው፤ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች ይህንን መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በፋይናንስና ቴክኒክ ያላቸውን ትብብር በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የሀገሪቱ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የደቡብ ኮሪያ የንግድ ምክትል ሚኒስትር ባይንግ ናኢ ያንግ አፍሪካ ሰፊ ወጣት የሰው ሃይልና ጥቅም ላይ ያልዋለ ሃብት ያላት በመሆኗ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም እንዳላት ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *