በኢትዮጵያ ቆይታ እያደረገ ያለው የፓኪስታን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑክ ቡድን የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንደስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል፡፡

ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ፣ ክቡር አምባሳደር ጀማል ባከር እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ የልዑክ ቡድኑን ጉብኝት የመሩ ሲሆን መንግስት ኢንቨስተሮችን ለመደገፍ ባደረጋቸው የህግ እና የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ ለቡድኑ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ከ70 በላይ አባላትን የያዘው ልዑክ ቡድኑ በፓርኮቹ ዘመናዊነት እና ውስጣቸው በያዙት ቴክኖሎጂ እንደተደነቁ ፓርኮቹን የመጎብኘት ዕድል ስላገኙ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸውም ገልፅዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *