Uncategorized

“ሁሉም ሸቀጥ ከጦር መሳሪያ በስተቀር (Everything But Arms – EBA)” ስለሚባለው ለ 49 ሃገራት ስለተፈቀደው የአውሮፓ ህብረት 🇪🇺 ታላቅ የንግድ እድል ሰምተው ያውቃሉ? ይህ የንግድ እድል ተግባር ላይ የዋለበት 22ኛ ዓመት በመጋቢት ወር ይከበራል!

በዚህ የንግድ እድል አማካኝነት ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ህብረት የምትልካቸው ሁሉም ምርቶች (ከመሳሪያ እና ጥይት በስተቀር) ከታሪፍ እና ከኮታ ነፃ ናቸው:: ለዚህ ኢትዮጵያ 🇪🇹 ላለፉት 22 ዓመታት በአውሮፓ ህብረት ነፃ፣ የባለ አንድ ወገን እና ያልተገደበ የገበያ መዳረሻ አግኝታለች። ስለ EBA የንግድ እድል የበለጠ ለማወቅ ከታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ፡፡

የፓኪስታን የንግድ እና የኢንቨስትመንት የልዑክ ቡድን አምስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ጀማል ባከር እንዲሁም ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ልዑክ ቡድኑን ተቀብለዋል፡፡ ከ70 በላይ የሚሆኑ አባላትን ያካተተው ልዑክ ቡድኑ በቆይታው ከተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በኢንቨስትመንት ዘርፉ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ እና የሀገራችንን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን እንደሚቃኝ ይጠበቃል፡፡

በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት በሚንቀሳቀስ የገንዘብ መጠን ላይ በድጋሚ ገደብ ሊጣል ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት በቀን ውስጥ ማንቀሳቀስ የሚቻለው የገንዘብ መጠን ላይ ያነሳውን ገደብ በድጋሚ የሚጥል መመሪያ አዘጋጀ። ረቂቅ መመሪያው የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች በአካውንታቸው ውስጥ መያዝ የሚችሉትን የገንዘብ መጠን ከ100 እስከ 233 በመቶ አሳድጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው ይህ ረቂቅ የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪነት ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ …

በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት በሚንቀሳቀስ የገንዘብ መጠን ላይ በድጋሚ ገደብ ሊጣል ነው Read More »

ዶላር በባንኮች በኩል እስከ 115 ብር እየተሸጠ ነው::

አሁን ባንኮች እያቀረቡበት ያለው ዋጋ ከጥቁር ገበያውም የበለጠ ሆኗል:: በሀገር ውስጥ ያለው ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች በተለይም የግሎቹ ምንዛሪን ለሚጠይቋቸው ደንበኞች የሚያስከፍሉት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለምንዛሪው እለታዊ መሸጫ ካወጣው የዋጋ ተመን በላይ መሆኑን ዋዜማ ካደረገችው ቅኝት መረዳት ችላለች። ለአንድ የአሜሪካ ዶላር ከግል ባንኮች እየተጠየቀ ያለው ኮሚሽንም ከ55 ብር እስከ 60 …

ዶላር በባንኮች በኩል እስከ 115 ብር እየተሸጠ ነው:: Read More »

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ከቻይና የፋይናንስ ተቋም ጋር ውይይት አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በቅርቡ በቤጂንግ ባደረገው ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከዋና ዋና የቻይና የፋይናንስ ተቋማት (FIs) እና አበዳሪዎች ጋር ተገናኝቷል። የልዑካን ቡድኑ ከቻይና ኤግዚም ባንክ፣ ከቻይና ኢንዱስትሪያልና ንግድ ባንክ፣ ከቻይና ልማት ባንክ፣ ከቻይና ኤክስፖርትና ብድር መድን ድርጅት/ሲኖሱር እና ከቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ/CIDCA ጋር ውይይት አድርጓል። የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እና FIs በተለያዩ ዘርፎች በመካሄድ ላይ …

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ከቻይና የፋይናንስ ተቋም ጋር ውይይት አካሂዷል። Read More »

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩን ጋር ተወያዩ።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር ቻይና የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን ስለምታደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ቻይና የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደምትሰጥ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በሀገራችን ያለውን የግብርና ኢንቨስትመንት ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ እንዲሰማሩ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ በውይይቱ ተገልጿል።