30 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አጥታለች ተብሏል

ዓለማችን በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገልጿል

30 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ።

ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመከታተል እና ሪፖርቶችን በማውጣት የሚታወቀው ኔት ብሎክስ የ2023 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከኢንተርኔት በመዝጋት ገቢ ካጡ ሀገራት መካከል ከሩሲያ በመቀጠል ከፍተኛ ገቢ ያጣች ሀገር ተብላለች።

ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት ውጪ በማድረጓ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታጣ ኢትዮጵያ ደግሞ 30 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ተደርገዋል።

ሆን ተብሎ በመንግስት እንደተወሰደ የተገለጸው ይህ ኢንተርኔት ማቋረጥ ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቷታል ተብሏል።

በአፍሪካ በጣም ቀርፋፋ የሞባይል ኢንተርኔት ያላባቸው ሀገራት

ሀገራት ኢንተርኔት አገልግሎቶችን የሚያቋርጡት በሶስት ምክንያት ነው የተባለ ሲሆን ተቃውሞዎችን ለማፈን፣ የሀሳብ ነጻነትን ለመገደብ እና የምርጫ ስራዎች እንዳይታወኩ በሚል እንደሆነም ተገልጿል።

25 የዓለማችን ሀገራት ኢንተርኔት አቋርጠዋል የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ ሁሉም ማሕበራዊ የትስስር ገጾች መታገዳቸው ተገልጿል።

የቀድሞ ስሙ ትዊተር ወይም ኤክስ ደግሞ ከሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል በብዙ ሀገራት ታግዷል ተብሏል።

ይህ ሪፖርት አዲሱ የፈረንጆቹ 2024 ዓመትን አይመለከትም የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራ የኢንተርኔት ገደቦች አሁንም እንደተጣሉ ናቸው።

በአማራ ክልል ካሳለፍነው ሀምሌ ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት በዚሁ ጊዜ እንደተቋረጠ ይገኛል።

ለስድስት ወራት በሚል የጣወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን አዋጁ ሊጠናቀቅ ቀሪ ሁለት ይቀሩታል።

በአጠቃላይ በ2023 ዓመት 747 ሚሊዮን ዜጎች በመንግስታት በተወሰዱ እርምጃዎች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጣቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ አል ዐይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *