የፓስፖርት ዋጋ ማሻሻያ ይፋ ተደረገ

አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት 5 ሺህ ብር አስቸኳይ ደግሞ 25 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል

በአዲሱ የዋጋ ዝርዝር ለእድሳት፣ ለጠፋ ፓስፖርትና ለእርማተ ከ13 ሺህ እስከ 40 ሺህ ብር ዋጋ ወጥቶላቸዋል

የኢትዮጵያ ኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርት ማውጣት እና ለማሳደስ የሚከፈለው ክፍያ ላይ ማሻሻያ መድረጉን አስታወቀ።

አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ 550/2024 መሰረት ለመደበኛ፣ ለአስቸኳይ፣ ለእድሳት፤ ለጠፋ እና እርማት ፓስፖርት አገልግሎቶች ከነሃሴ 1 ጀምሮ 2016 ዓ/ም ተግባራዊ የሚሆን የዋጋ ማሻሻያ ክፍያ ዝርዝር አድርጓል።

በዚህ መሰረት ከነገ ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት ለማዉጣት 5 ሺህ ብር የሚያስከፍል ስሆን፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 25 ሺህ ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖር 20 ሺህ እንዲሆን ተደርጓል።

ለፓስፖርት እድሳት እና ገጽ ላለቀባቸውም ተመሳሳይ ዋጋ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም በመደበኛ 5 ሺህ ብር፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 25 ሺህ ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖር 20 ሺህ እንዲሆን ተደርጓል።

እድሳት ለሚፈልጉ እና እርማት ለሚያስፈልጋቸው መደበኛ 12 ሺህ 500 ብር፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 32 ሺህ 500 ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖርት 27 ሺህ 500 ብር ሆኗል።

ፓስፖርቱ ቀን ያለውና የበላሸ ከሆነ ደግሞ መደበኛ 13 ሺህ ብር፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 33 ሺህ ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖርት 28 ሺህ ብር መደረጉ ተመላክቷል።

ፓስፖርቱ ቀን እያለው የተበላሸ እርማት ለሚፈልጉ መደበኛ 20 ሺህ 500 ብር፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 33 ሺህ ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖርት 35 ሺህ 500 ብር ሆኗል።

ለጠፋ ፓስፖርት መደበኛ 13 ሺህ ብር፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 33 ሺህ ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖርት 28 ሺህ ብር ተደርጓል።

የጠፋ ፓስፖርት እርማት ደግሞ መደበኛ 20 ሺህ ብር፤ በ2 ቀን የሚደርስ አስቸኳይ ፓስፖርት 40 ሺህ 500 ብር እንዲሁም በ5 ቀን የሚደርስ አስቸኳ ፓስፖርት 35 ሺህ 500 ብር ተደርጓል።

ምንጭ፦ አል አይን ኒውስ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *