የጉምሩክ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል ካርጎ ትራኪንግ ቴክኖሎጂ አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ።

የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ካሁን ቀደም ይህንን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረቶች ቢደረጉም በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።

መንግሥት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ደረጃ ላይ መደረሱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ቴክኖሎጂው ተግባራዊ እንዲደረግ ጥረት ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚንስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህ ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል ብለዋል።

ዶክተር ዓለሙ የዚህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን ተግባራዊ መደረግ የጭነቶችን ደህንነት በመጠበቅ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ያግዛል ሲሉም ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኢንተሊጀንስ፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን፣ የአዲስ አበባ ዩኑቨርስቲ እና የሌሎች ባለድርሻ አካላት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል።

ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ አማካይነት የበለጸገ መሆኑም ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *