የጅማ አካባቢን የተፈጥሮ አቅም ያማከለ ኢንቨስትመንት እንዲኖር ይሠራል – ኮርፖሬሽኑ

በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአካባቢውን የተፈጥሮ እምቅ አቅም ያማከለ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር እንሰራለን ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴን እና ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር የተፈጠረውን የገበያ ትስስር ተመልክተዋል።

እንዲሁም በፓርኩ ያሉ አምራች ኩባንያዎች ስላሉበት የምርት እንቅስቃሴ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የወጪ እና የተኪ ምርት ጉዳዮች ላይ ከባለሃብቶቹ ጋር ተወያይተዋል።

ከውይይቱ በኋላም በቀጣይ በፓርኩ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን÷ በተለይም በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ዘርፍ ለመሰማራት በአካባቢው ያለው የተፈጥሮ እምቅ አቅም ምቹ መሆኑን አመላክተዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *