የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባዔና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ።

20ኛዉ የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች እና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን ጉባዔና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ይህን አስመልክቶ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በመጪዉ ጥር ወር ላይ የሚካሄደው ጉባዔ የኢትዮጵያ ቡና በአፍሪካ እና በዓለም ገበያ ይበልጥ ለማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጥር ገልጿል።

“Specialty Coffee at Origin” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ጉባዔዉ ላይ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የዓለም አቀፍና የቀጠናዊ የዘርፉ ባለሞያዎችን በአንድ ጣሪያ ስር አሰባስቦ ለማወያየት ታቅዷል።

የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባዔና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን “IACO” ከጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በዚሁ ጊዜ የመጀመሪያዉ የአፍሪካ ቡና ሳምንት የሚካሄድ መሆኑ ተሰምቷል።

ምንጭ፡- FBC

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *