የቻይና አየር መንገዶች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ሳምንታዊ በረራ ወደ 50 እንዲያሳድጉ ተፈቀደ

የቻይና አየር መንገድ ሳምንታዊ የአሜሪካ በረራ 35 ነበር

ከኮቪድ 19 በፊት የቻይና አየር መንገዶች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ሳምንታዊ በረራ 150 ነበር

የቻይና አየር መንገዶች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ሳምንታዊ በረራ ወደ 50 እንዲያሳድጉ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የአሜሪካ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ለቻይና አየር መንገዶች የተፈቀደው ሳምንታዊ የበረራ ቁጥር ከኮሺድ 19 በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር አንድ ሶስተኛው መሆኑንም ሮይተርስ ዘግቧል።

አሁን ላይ የቻይና አየር መንገዶች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ሳምንታዊ በረራ 35 ሲሆን፣ ከፈረንጆቹ መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ ወደ 50 ያድጋል ተብሏል።

በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የንግድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር መጨመሩ አሜሪካ እና ቻይና በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ወደ መደበኛ የመመለስ ሂደት ውስጥ ወሰኝ እርምጃ መሆኑን የአሜሪካ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

በፈረንጆቹ 2020 የኪቪድ 19 የጉዞ ክልከላ ከመጣሉ በፊት የአሜሪካ እና የቻይና አውሮፕላኖች በሳምንት ከ150 በላይ የደርሶ መልስ በረራዎችን ያደርጉ ነበር።

ሆኖም ግን ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ እስከ ነሃሴ 2023 ድረስ የቻይና እና የአሜሪካ አየር መንገዶች የሚያደርጉት ሳምንታዊ በረራ በሳምንት ከ12 አይበልጥም ነበር ተብሏል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *