የሀምሌ 26 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ምን ይመስላል?

ዳሽን፣ አዋሽ፣ አባይ እና ኦሮሚያ ባንክ የ1 ዶላርየመግዣ ዋጋን 90 ብር አድርሰዋል

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ ካደረገች በኋላ በ1 ዶላር ከ30 ብር በላይ ጭማሪ ታይቷል

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ ከ25 እስከ 32 ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቷል።

ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የሀምሌ 26 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።

በዚህም መሰረት አዋሽ ባንክ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ90.0029 ብር እየተገዛ በ94.5011 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ዳሽን ባንክም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ90.7899 ብር እየተገዛ በ98.0531ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።

በኦሮሚያ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ90.6055 ብር እየተገዛ በ94.6827 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግል ባንኮች ዝቅ ያለ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አውጥቷል። ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ83.9413 እየገዛ በ85.6201 ብር እየሸጠ ነው።

ምንጭ፦ አል ዐይን ኒውስ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *