ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በግብርና ዘርፍ ኢንደስትሪን ማዕከል ያደረገ ልማት እንዲጠናከር ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግብርና ዘርፍ ትብብርን ማስፋት ብሎም ኢንዱስትሪን ማእከል ያደረገ ልማትን ማጠናከር እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዕለቱ ውሎ ሁለተኛ መርሐ-ግብር በ3ኛው ቢአርአይ ከፍተኛ ጉባዔ ላይ “Connectivity in an Open Global Economy” በሚል ጭብጥ ንግግር ማቅረብ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው በኢትዮጵያ የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭን ስኬታማ ልምድ አጋርተዋል::

በግብርና ዘርፍ ትብብርን ማስፋት ብሎም ኢንዱስትሪን ማእከል ያደረገ ልማትን ማጠናከር እንደሚገባም ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *