የፓኪስታን የንግድ እና የኢንቨስትመንት የልዑክ ቡድን አምስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ጀማል ባከር እንዲሁም ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ልዑክ ቡድኑን ተቀብለዋል፡፡

ከ70 በላይ የሚሆኑ አባላትን ያካተተው ልዑክ ቡድኑ በቆይታው ከተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በኢንቨስትመንት ዘርፉ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ እና የሀገራችንን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን እንደሚቃኝ ይጠበቃል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *