የፌስቡክ እናት ሜታ ኩባንያ በአንድ ቀን 20 ቢሊዮን ዶላር ማጣቱ ተገለጸ

በሜታ ኩባንያ ስር የነበሩት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ለአንድ ሰዓት ያህል እክል ገጥሟቸው ነበር።

በዚህ እክል ምክንያት የሜታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ዝቅ ብሏል

የፌስቡክ እናት ሜታ ኩባንያ በአንድ ቀን 20 ቢሊዮን ዶላር ማጣቱ ተገለጸ።

በትናንትናው ዕለት በሜታ ኩባንያ ስር የነበሩት ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ኢንስታግራም ትሬድስ የተሰኙት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋርጠው ነበር።

በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ላይ በገጠመው በዚህ እክል ምክንያት የሜታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ መቀነሱ ተገልጿል።

በፌስቡክ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ከአገልግሎት ውጪ የሆነበት ዕለትም የትናንትናው ማለትም የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ሆኖ ተመዝግቧልም ተብሏል።

ፌስቡክን ጨምሮ የሜታ መተግበሪያዎች ላይ ያጋጠመው ምንድን ነው?

በእነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ምክንያት በርካቶች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው እንደተጠለፈባቸው መደምደሚያ ላይ የደረሱ ሰዎች እና ተቋማትም ቀላል እንዳልነበር መናገራቸው ተገልጿል።

በዚህ መስተጓጎል ምክንያትም አንድ የሜታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ የ7 ነጥብ 7 ዶላር ዋጋ ቅናሽ እንዳሳየ ሲገለጽ በአጠቃላይ በአንድ ሰዓት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር አጥቷል ተብሏል።

የሜታ ኩባንያ አጠቃላይ ሀብት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ከዋትስ አፕ ውጪ ያሉት ቀሪ መተግበሪያዎች አገልግሎታቸው ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋርጦ ነበር።

የሜታ ኩባንያ መተግበሪያዎች በመላው ዓለም ያጋጠመ ቢሆንም በአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና ፣ ሜክሲኮ እና ግብጽ ብዙ ተጠቃሚዎች ከአገልግሎት ውጪ ሆነው ነበር ተብሏል።

ምንጭ፦ አል አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *