የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩን ጋር ተወያዩ።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር ቻይና የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን ስለምታደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ቻይና የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደምትሰጥ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በሀገራችን ያለውን የግብርና ኢንቨስትመንት ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ እንዲሰማሩ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ በውይይቱ ተገልጿል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *